መኑ ይእቲ ሙዳየ ግእዝ/Who is Mudaye Geez?
፩.ሙዳየ
ግእዝ:
የስሟ
ትርጓሜ
✍ሙዳየ ግእዝ ፣ ሙዳይ እና ግእዝ ከሚሉ ሁለት የግእዝ ቃላት የተመሰረተ ሲሆን:-
፩. ሙዳይ
👉ሙዳይ ማለት በቁሙ ሙዳይ ወይም በተመሳሳይ ፍች በመጠን አነስ ያለ አገልግል ማለት ነው።👉ሙዳይ አማናዊ የህይወት ምግብ ያገኘንባት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ነች።
✍ሙዳይ/አገልግል መንገደኛ ስንቅ ይዞ ከስጋዊ ድካሙ የሚያርፍባት ሲሆን ሙዳይ እመቤታችንም በኃጢአት ወጥመድ ተይዞ የንስሐ መንገደኛ የሆነ አዳም አማናዊ ስንቅ ክርስቶስን ይዛ ተገኝታለችና ከዘላለማዊ ድካም አርፎባታል።
፪. ግእዝ
👉ግእዝ/ግዕዝ በአልፋው 'አ' እና በዐይኑ 'ዐ' ሲጻፍ የተለያየ ትርጉም ይሰጣል። ይኸውም:-➕"ግእዝ" የሚለው ቃል ገአዘ፣ግእዘ ከሚለው ስርወ ቃል የተገኘ ሲሆን አወጣጡም ዘመድ ዘር (ስም) ይባላል። ትርጉሙም አንደኛ፣የመጀመሪያ፣ቀዳማይ ማለት ነው።
በስምነቱም👇👇👇
፩. የፊደል ስም - ግእዝ የሚለው ቃል የፊደል ስም ሲሆን የመጀመሪያ፣ ፈርጅና ቅጥያ የሌለው ፣ ከዘመነ አብርሃ ወአጽብሐ በፊት የነበረው የመጀመሪያ ፊደል ማለት ነው፡፡
፪. የንባብ ስም፡- በልሳነ
ግእዝ የሥርዓት ንባብ መሠረት
ሦስት የንባብ ዓይነቶች ማለት
ግእዝ ፣ ውርድ እና
ቁም፣ ከእነዚህም ውስጥ ግእዝ
የመጀመሪያ
ማለት ነው፡፡
፫.የዜማ ስም፡- ኢትዮዽያዊው
ሊቅ ቅዱስ ያሬድ በመንፈስ
ቅዱስ ተቃኝቶ ከደረሳቸው የዜማ
ስልቶች
ማለትም
ግእዝ ፣ዕዝል እና ዓራራይ
ውስጥ አንዱ በአብ የሚመስለው
የዜማ ስልት ግእዝ ነው፡፡
፬.የቋንቋ ስም፡- የመጀመሪያ
ቋንቋ ፣አዳማዊ ቋንቋ ፣
ሴማዊ ቋንቋ ጥንታዊ ቋንቋ
ማለት ነው::
፭. የሀገር ስም
:- ለመጀመሪያ
ጊዜ ከዓለመ እስያ ተነስቶ
ቀርነ አፍሪቃ ወደሆነችው ምድረ
ኢትዮዽያ
የገባው
የሰው ዝርያ ነገደ ኦሪት
በመባል
ይታወቃል፡፡
የመጣበት
ዘመንም
በ፩ሺ፫፻፴
1330 ዓ.ዓ እንደሆነ ተረጋግጧል።
የነገዱም
አለቃ ኦሪ(አራም) ይባላል፡፡
ከዘመነ
ሥጋዌ ሺ ፬፻፸ 4470 ዘመን
የቀድማል
ከዚህም
ነገድ ፳፮ ሰዎች በተከታታይ
ነግሰዋል፡፡ለ፳፪፻፶፮
2256 ዓ.ዓ በዘመነ ኖኅ
በመጨረሻው
ንጉሥ በሶሊማን ታጊ ጊዜ
በማየ አይኅ (በጥፋት ውሃ)
ጠፍተዋል
ኢትዮዽያ
ከማየ አይኅ በኃላ ፭፻፴፮
531 ዓመት በምድረ በዳነት ኑራለች
በ፳፯፻፹፯
2787 ዓ.ዓ ከበኩረ አበው
አለው በ፲ኛው ሐረግ የሚገው
የታላቁ
ጻድቅ የኖኅ ልጅ ካም
ምድረ ኢትዮዽያን ወረሰ፡፡ ካምም
ኢትዮዽያን
፪፮ ዓመት በበላይነት አስተዳድሯታል፡፡
ከእሱ በኃላ ልጆቹ ፯፻፵፯
747 ዘመን ገዝተዋል፡፡ ከእነሱም የአንዱ
ስሙ አቢሲኒስ (አቢስ) የባል
ስለ ነበር ከሱ ስም
ጋር በተያያዘ አቢሲኒያ ተብላ
ተጠርታለች፡፡
በዚህም
ጊዜ ቋንቋዋ ልሳነ ሳባ
ነበር (ደብረ ነገስት) በ፴፭፻፲
3510 ዓ.ዓ ደግሞ የካም
ወንድም
የሴም ወገኖች ነገድ ዮቅጣን
ከደቡብ
ዐረብ ወደ ቅድስት ሀገር
ኢትዮጵያ
መጡ፡፡
የመጡበትም
ሀገር በብሔረ ዐረብ ግእዝ
ከሚባል
አውራጃ
ነው፡፡
ቋንቋቸውም
በሀገራቸው
ስም ግእዝ ተብሏል፡፡
➕"ግዕዝ" የሚለው ቃል ግን
አግዐዘ:
ነጻ
አወጣ፣አዳነ ከሚለው የግእዝ
ስርወ ቃል የተገኘ ሲሆን
ትርጉሙም
ነጻነት፣ድህነት
የሚል ይሆናል።
✍ነጻ አወጣ👉"ፈቀደ እግዚእ ያግዕዞ
ለአዳም"
እንዳለ
ሊቁ በውዳሴ ማርያም ዘሰኑይ
✍
አዳነ👉"አግዐዘነ እምኃጢኣት ወሞት
ሮሜ ፰:፪" እንዳለ
ብርሀነ
ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ።
✅በመሆኑም ሙዳየ ግእዝ ስንል ጥንታዊ እና አዳማዊ ቋንቋ የሆነውን ግእዝ በውስጧ የያዘች ራስ ጠል ከሆነ የቋንቋ ርሀባችን የምንፈወስባት፣ ከድካማችን የምንታደስባት፣ እኛነታችን የምንመለከትባት መስታወታችን፣ ከአላወቂነት ወደ ሊቅነት የምንወጣባት መሰላላችን የግእዝ ሙዳይ ማለታችን ነው።
፪.⛑ ሙዳየ ግእዝ ማነች ? ⛑
ሙዳያችን ሙዳያችሁ ሙዳየ ግእዝ በኤግል ቋንቋ፣ ኮምፒዩተር እና ምህንድስና ሶፍትዌር
ማሰልጠኛ ተቋም
አዘጋጅነት ተሰናድታ የምትቀርብ፣ ግእዝን ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ፣ ቅድስት ቤተክርስቲያን በነጻ ያደለቻትን ሀብት በነጻ ለማደል የተነሳች፣ ከየትኛውም ክፍላተ አህጉር የሚታደሙ ልጆቿን በቀለጠፈ እና ዘመኑን በዋጀ፣ ለአፍ በሚቀል መልኩ ለመመገብ ጉንብስ ቀና እያለች ያለች ልዩ እና ብቸኛዋ የግእዝ ማሰልጠኛ ሙዳይ ነች።
አዘጋጅነት ተሰናድታ የምትቀርብ፣ ግእዝን ወደ ቀደመ ክብሩ ለመመለስ፣ ቅድስት ቤተክርስቲያን በነጻ ያደለቻትን ሀብት በነጻ ለማደል የተነሳች፣ ከየትኛውም ክፍላተ አህጉር የሚታደሙ ልጆቿን በቀለጠፈ እና ዘመኑን በዋጀ፣ ለአፍ በሚቀል መልኩ ለመመገብ ጉንብስ ቀና እያለች ያለች ልዩ እና ብቸኛዋ የግእዝ ማሰልጠኛ ሙዳይ ነች።
⛪️ይሁን እንጂ ከላይ ባጭሩ ለመግለጽ የተሞከረውን ሀሳቧን ለማሳለጥ እና ግቧን የተሳካ ለማድረግ ማንኛውንም ዘመኑ የደረሰባቸውን ቴክኖሎጂዎች ለምሳሌ ያህል Telegram, Zoom, Youtube, Facebook , WhatsApp,
Slack...ሌሎችንም በመጠቀም ተደራሽነቷን ለማስፋት ታጥቃ የተነሳች ቤተ ግእዝ ነች::
፫. ራእይ እና ተልእኮ
ራእይ
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በጥንታዊው የግእዝ ቋንቋ የተሰነዱ የቤተ ክርስቲያን ብሎም የሀገር ሀብቶችን በቀላሉ መርምሮ ከመረዳት አልፎ መላው ኢትዮጵያዊያን ልሳነ ግእዝን እንደ አፍ መፍቻ ቋንቋ ሲግባቡበት እና ሲጠቀሙበት ማየት።
ተልዕኮ
የተለያዩ ዘመኑ የደረሰባቸውን የቴክኖሎጂ ውጤቶች በመጠቀም ዕንቁ አባቶቻችን ያስተማሩንን የግእዝ ቋንቋ ቀላል ፣ ቀልጣፋ እና ለአፍ በሚቀል መልኩ ውድ ኢትዮጵያዊያን የት እና መቼ እንማር ብለው ሳይቸገሩ ባሉበት ማድረስ እና በየዓመቱ ብዛት ያላቸው የግእዝ ቋንቋ ተናጋሪዎችን ከተለያዩ አህጉረ ዓለማት ማፍራት።
፬.💐በእንተ ሙዳየ ግእዝ/ስለ ሙዳየ ግእዝ💐
፩.መዓርጋተ ሙዳየ ግእዝ(የሙዳየ ግእዝ የስልጠና ደረጃዎች)
በሙዳየ ግእዝ የሚሰጠው የግእዝ ቋንቋ ስልጠና በውስጡ በሚይዛቸው የስልጠና ይዘቶች መሰረት ፬ መዓርጋት (ደረጃዎች) አሉት። እነዚህም:-
1. ቀዳማይ ሙዳየ ግእዝ
2. ካልኣይ ሙዳየ ግእዝ
3. ሣልሳይ ሙዳየ ግእዝ
4. ራብዓይ ሙዳየ ግእዝ
ምሳሌነታቸውም:-
፩ኛ. በ፬ቱ አፍላጋት ግዮን፣ ጤግሮስ፣ ኤፍራጥስ እና ኤፌሶን ይመሰላሉ።
፬ቱ አፍላጋት ዓለምን እየተዘዋወሩ እንደሚያረኩ ይህችም የግእዝ ሙዳይ ጌታዋ፣ ፈጣሪዋ መድኅነ ዓለም ክርስቶስ በረዳት መጠን በዘመኑ ቴክኖሎጂ ታግዛ ግእዝን ለተጠሙ ምዕመናን ፬ቱን ደረጃዎች ተጠቅማ ታረካለችና።
፪ኛ. በ፬ቱ ወንጌላውያን ይመሰላሉ ።
፬ቱ ወንጌላውያን የምስራች ወንጌልን ለዓለም በመስበክ አልጫ የሆነውን ዓለም በክርስቶስ ህያው ቃል እንዳጠፈጡ እኒህም መዓርጋተ ሙዳየ ግእዝ ጥንታዊውን የግእዝ ቋንቋ በመላው ዓለም ለሚገኙ ህዝበ ክርስቲያን ባሉበት በማዳረስ መጻህፍትን መመርመር፣ ሃይማኖታቸውን በሚገባ ማወቅ፣ መረዳት አለፍ ብሎም የቅዱሳን ምድር ምድረ ኢትዮጵያ በቀደምት ሊቃውንት ልጆቿ ዘግባ ያስቀመጠችልንን ሀብት እራሳችን ችለን እንድንመገብ ትረዳናለችና።
እራሳችንም ችለን ማለታችን፣
ለምሳሌ፣
👉አንድ ህጻን በልጅነቱ አፍ ሳይፈታ፣ የምግብን ጥቅም በውል ሳይረዳ ባለበት የእድሜ ክልል ውስጥ ውድ እናቱ ለእርሱ የሚጠቅመውን በመጠን፣ በአቅሙ፣ ለጤናው ሊስማማ በሚችል መልኩ ፈትፍታ ትመግበዋለች። የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ባለውለታዎች ሊቃውንትም እያደረጉ ያሉት ይህንን ነው። ለግእዝ አፍ ያልፈታን ህጻናት ከመሆናችንም የተነሳ መጻሕፍትን ከተጻፉበት የግእዝ ቋንቋ ለእኛ ለቀለም ልጆቻቸው በሚስማማ መልኩ ወደ አማርኛ እና ሌሎችም የአፍ መፍቻ ቋንቋዎች በመተርጎም ፈትፍተው ያጎርሱናል ማለት ነው።
ተወዳጆች ሆይ ከእንግዲህስ ሙዳየ ግእዝ እናታችሁ የሕጻንነት እድሜኣችሁን ጨርሳችሁ ጎልማሳ ሆናችኋልና፣ ክፉ እና ደጉንም ለይታችኋልና፣ ግእዝ ስንቃችሁን ከሙዳያችሁ ላይ ዘግናችሁ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከአባቶቻችሁ እግር ስር ስርዓት እና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እራሳችሁን ችላችሁ ተመገቡ ትላችኋለች።
፪. የሙዳየ ግእዝ የስልጠና ጊዜ ቆይታ
አንድ የሙዳየ ግእዝ ሰልጣኝ ስልጠናውን አጠናቀቀ የሚባለው ፬ቱንም መዓርጋት መውሰድ ሲችል ነው። ይኸውም እያንዳንዳቸው ሁለት ወር የጊዜ ቆይታ ይኖራቸዋል። በአጠቃላይ የሙዳየ ግእዝን የግእዝ ቋንቋ ስልጠና ለማጠናቀቅ እና ብቁ ለመሆን የ8 ወራት ወይንም ፬ ተከታታይ ስልጠናዎችን መውሰድ ይገባል ማለት ነው።
፫.የስልጠና ክፍያ- ነጻ
እነሆ ሙዳየ ግእዝ ከሊቃውንት አባቶቿ ያለምንም ክፍያ በነጻ ያገኘችውን ሀብት በነጻ ለማደል ዝግጅቷን አጠናቃለች። ብቸኛው ትርፏም በነጻ ያገኘችውን በነጻ በመስጠት የእናት ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ውለታ ለመመለስ የድርሻዋን መወጣትና ከህሊና ወቀሳ ነጻ መሆን ነው።
፬. ሙዳየ ግእዝ መቼ እና የት?
የት=ባሉበት።
መቼ=በትርፍ ሰዓትዎት።
👉የሙዳየ ግእዝ ስልጠና ሙሉ በሙሉ የኦንላይን ስልጠና ከመሆኑ የተነሳ በማንኛውም ጊዜ እና ሰዓት የትም ቦታ ሆነው በተሰጠው መርሀ ግብር መሰረት ማግኘት ይችላሉ።በሰልጣኞች ፈቃድ ላይ የተመሰረቱ አንዳንድ የገጽ ለገጽ ትምህርቶች የሚሰጡ ቢሆንም ይህንን በቀጥታ ለመሳተፍ ለማይችሉ ሰልጣኞቻችን ዘመኑ ባመጣቸው ቴክኖሎጂዎች ተቀርጸው እንዲያገኟቸው ይደረጋል። ስለሆነም የሚያልፋቸው ነገር አይኖርም።
👉በተጨማሪም ስልጠናው ከአባላት ጋር ቅርብ በሆነ እና ሰልጣኞችን እርስ በእርሳቸው ሀሳብ እንዲለዋወጡ፣ ከእነርሱ ያለፈውን ጥያቄም ወደ ሙዳየ ግእዝ በቀላሉ እንዲያመለክቱ በሚያስችል ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀ ፕላትፎርም የሚሰጥ ይሆናል።
፭. ሙዳየ ግእዝን ለመሰልጠን ሰልጣኞች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1. የግእዝ ቋንቋን ለመሰልጠን ሰልጣኞች ሙሉ በሙሉ የውስጥ ተነሳሽነት፣ ቆራጥነት እና የቋንቋው የእኔነት ስሜት ሊኖራቸው ይገባል።
2. ሰልጣኞች ስልጠናውን ያለምንም ማቆራረጥ ለመውሰድ የሚያስችል የእጅ ስልክ ወይንም ኮምፒዩተር ሊኖራቸው ይገባል።
3. የስልጠና ህግና ስርዓት ወደፊት የሚገለጽ ቢሆንም አንድ ሰልጣኝ በሙዳየ ግእዝ የስልጠና ማዕቀፍ ታቅፎ የግእዝ ቋንቋን ለመሰልጠን ግብረ ገብ እና ያወቀውን፣ የተረዳውን ለወንድም እህቶቹ በቅን ልቡና ለማካፈል የተዘጋጀ መሆን ይገባዋል።
4. የሙዳየ ግእዝ ሰልጣኝ ቋንቋውን ለማጥናት ለራሱ ከሚወስዳቸው የጥናት ክፍለ ጊዜዎች በተጨማሪ የቀጥታ ትምህርቶችን ለመከታተል እና ከወንድም እህቶቹ ጋር ለማጥናት የሚሆን ቢያንስ በሳምንት 2 ሰዓት የሚኖረው መሆን አለበት።
፮. የስልጠና አሰጣጥ እና የማብቃት ሂደት
1.በተ.ቁ ፭ የተገለጹትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችል ማንኛውም ሰልጣኝ የቀዳማይ ሙዳየ ግእዝ ስልጠናን መውሰድ ይችላል።
2. በእያንዳንዱ የሙዳየ ግእዝ የስልጠና መዓርጋት የግል ስራዎች፣ የቡድን ስራዎች እንዲሁም ምዘናዎች የሚኖሩ ይሆናል። በመሆኑም የቀዳማይ ሙዳየ ግእዝን ስልጠና ከመቶው ስድሳ (60%) ማምጣት ያልቻለ ሰልጣኝ ወደ ቀጣይ የሙዳየ ግእዝ መዓርግ ሊሸጋገር አይችልም።
3. በተለያዩ አጋጣሚዎችና የማይመች ሁኔታ ላይ ሆነው ያቋረጡ ሰልጣኞች ተመልሰው ለመቀጠል ቢፈልጉና ቢያመለክቱ ባቆሙበት የሙዳየ ግእዝ ደረጃ እንዲቀጥሉ እድሉ የሚመቻችላቸው ይሆናል።
4. ስልጠናውን በተከታታይ ሰልጥነው ላጠናቀቁ ሰልጣኞች የስልጠና ማጠናቀቂያ የምስክር ወረቀት ከሙዳየ ግእዝ ይሰጣቸዋል።
፯.የአገልግሎት አድማስን ማስፋት
፩. ይህን የተቀደሰ ሀሳብ ሙዳየ ግእዝ ጸንሳ፣ ፱ ወር ከ፭ ቀን በማህፀነ ህሊናዋ ተሸክማ፣ በብዙ ጭንቀት እና ህማም አምጣ ትውለደው እንጂ ከዚህች ቀን በኋላ ግን ከልዑል እግዚአብሄር በታች ይህን አገልግሎት ኮትኩቶ የማሳደግ ሙሉ ኃላፊነት የሙዳየ ግእዝ ቤተሰቦች አለፍ ሲልም ግእዝን ለማለምለም ውሳጤ ህሊናቸው የሚቀሰቅሳቸው ቅን አሳቢዎች ምዕመናን ይሆናል።
፪. ⛑ #በመጨረሻም አንድ የሙዳየ ግእዝ ሰልጣኝ ስልጠናውን አጠናቆ ሲጨርስ እኔ ጨርሻለሁ ብሎ ከሙዳየ ግእዝ መውጣት ሳይሆን ሙዳየ ግእዝ ባዘጋጀችለት ፕላትፎርም ከእርሱ በኋላ የሚሰለጥኑ እኅት ወንድሞቹን ለማገዝ የእርሱንም እውቀት ለማዳበር በሳምንት ቢያንስ 30 ደቂቃ ሊሰጥ የሚችል ቅን ታዛዥ መሆን ይኖርበታል።